
አህፅሮት ኢትዮጵያ ዳፕና ዩሪያ የተባሉ ማዳበሪያዎችን ለረጅም ጊዜ ስትጠቀም ብትቆይም በሀገሪቱ ያለው የአፈር ዓይነትና የስነ-ምህዳር ልዩነት መስፋት ሌሎች ማዳበሪያዎችን ማለትም የተለያዩ ማይክሮ ንጥረ-ነገሮችን ጭምር የያዙ ቅይጥ ማዳበሪያዎችን መጠቀም እንዳለባት ግንዛቤ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም የአፈርን ዓይነት፣ የተለያዩ ሰብሎችንና አካባቢን ግምት ውስጥ ያስገባ የተለያዩ አዳዲስ ማዳበሪያዎችን የመገምገምና አማራጭ ማዳበሪያ ለተጠቃሚው የማቅረብ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ምክንያት ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ የተባለ አዲስ ማዳበሪያ ውጤታማነቱንና አዋጭነቱን ለመለየት በመስኖ ውሃ በመጠቀም በሚመረት የቲማቲም ሰብል ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል ከ2010-2011 ዓ.ም. ጥናቱ ተከናውኗል፡፡ ለዚህም ጥናት አዲሱን ማዳበሪያ በሦስት የተለያየ መጠን አሁን ለቲማቲም ሰብል ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው የኬሚካል ማዳበሪያ ምክረ-ሃሳብ ጋር አቀናጅቶ ማሳ ላይ በመጨመር ተከናውኗል፡፡ የጥናቱ ውጤት አንደሚያሳየው ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ ማዳበሪያን መጨመር የቲማቲም ምርት ላይ ጥሩ የሚባል መሻሻል አሳይቷል፡፡ በተጨማሪም ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ ማዳበሪያን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ምክረ-ሃሳብ ጋር አቀናጅቶ ማሳ ላይ መጨመር የቲማቲም ምርትን እንደጨመረና የገብያ አዋጭነቱም ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጥናት ማጠቃለል የሚቻለው ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ ማዳበሪያን ጥናቱ ከተካሄደባቸው አካባቢዎች እንደ ደጓሚ ማዳበሪያ መጠቀም እንደሚቻል ነው፡፡ Abstract Ethiopia was using urea and DAP fertilizers as sources of nitrogen and phosphorous nutrients for a long time. However, the crop and agro-ecology diversity in the country demand more multi-nutrient blends including micronutrients than nitrogen and phosphorus. This increasing demand requires evaluation of different fertilizer resources based on soil type, crop species, and location to provide new alternative fertilizer products to the Ethiopian production system. Cognizant of this fact, an experiment was conducted to evaluate the efficacy of Tradecorp AZ Bentley plus as a supplementary fertilizer to improve yield of tomato under irrigation in different areas in East Shoa Zone of Oromia, during 2018-2019. The experiment consisted of five treatments ( Control, recommended fertilizer, recommended fertilizer + 1.8 kg product, recommended fertilizer + 3.0 kg product and recommended fertilizer + 4.2 kg product) laid out in randomized complete block design (RCBD) with four replications. The results revealed that application of Tradecorp AZ Bentley plus fertilizer product improved tomato marketable and total yields at testing sites. In addition, the application of Tradecorp AZ Bentley plus as supplementary fertilizer in combination with the recommended fertilizer rate attained acceptable net returns of tomato at both locations. Hence, Tradecorp AZ Bentley plus is recommended as supplemental fertilizer for tomato producing farmers in testing areas. Keywords: East Shoa, Tomato yield, Tradecorp AZ Bentley plus
አህፅሮት ይህ ጥናት የተካሄደው ዘጠኝ (አራት ከውጪ የገቡ እና አምስት ከሀገር ውስጥ የተሰበሰቡ) የሙዝ ዝርያዎችና አንድ በመመረት ላይ የሚገኝ የማወዳደሪያ ዝርያ በአራት የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሁለት የምርት ዓመታት ያላቸውን የዕድገት፣ ምርት እና ጥራት ሁኔታ ለመገምገም ነበር፡፡ በእያንዳንዱ የሙከራ ቦታ እያንዳንዱ ዝርያ ሶስት ጊዜ በተለያየ ረድፍ ተተክሎ አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ተገምግመዋል፡፡ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በተክል ቁመት፣ ተተክሎ ማበብ እስከሚጀምር እና ተተክሎ ምርት እስከሚደርስ በሚወስደው ጊዜ፣ በአምባዛ (ዘለላ) ክብደት፣ በፍሬ ውፍረት፣ በፍሬ ርዝመት፣ በፍሬ ክብደት፣ በምርት መጠን፣ በልጣጭ ውፍረት፣ የሚበላው ክፍል ከልጣጩ ጋር ባለው ጥምርታ፣ በሚሟሙ ጠጣሮች መጠን፣ በአሲድ መጠን፣ በፒኤች፣ በፍሬ እርጥበት እና በፍሬ የአመድ ይዘት መጠን በዝርያዎች መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተመዝግቧል፡ እንደአጠቃላይ ዝርያዎቹ አጭርና ወፍራም ተክል (ግንድ) ነበራቸው፡፡ ዝርያዎቹ ተተክለው እስኪያብቡ ከ243.8 እስከ 316.8 ቀናት እንዲሁም ተተክለው ምርታቸው እስኪሰበሰብ ከ374.4 እስከ 446.7 ቀናት ወስዶባቸዋል፡፡ የሁሉም የሙከራ አካባቢዎች አማካይ የምርት መጠን ከ43.67 እስከ 52.46 ቶን በሄክታር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አምስት ዝርያዎች ከማወዳደሪያው ዝርያ አኳያ ተወዳዳሪ (ተመሳሳይ) የሆነ ምርት አስመዝግበዋል፡፡ በስሜት ህዋሳት አማካኝነት በተካሄደ የትንተና መረጃ መሰረት ሁሉም ዝርያዎች በቀማሾች ዘንድ ተመራጭ ሆነዋል፡፡ ከማወዳደሪያ ዝርያው አኳያ እጩ ዝርያዎች ከፍተኛ የሚሟሙ ጠጣሮች መጠን፣ ፎስፎረስ እና ፖታሲየም እንዲሁም አነስተኛ የአሲድ መጠን አስመዝግበዋል፡፡ የፍሬ እርጥበትና የአመድ ይዘት መጠን እንደቅደምተከተላቸው ከ71.53 እስከ 76.56 በመቶ እና ከ2.5 እስከ 3.36 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የዕድገት፣ የምርትና የጥራት መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ‘ሌዲ ፊንገር’ እና ‘ድንኬ-1’ የተባሉት ዝርያዎች በዋና ዋና የሙዝ አምራች አካባቢዎች ወደምርት እንዲገቡ ምክር ተሰጥቷል፡፡ Abstract A study was conducted to evaluate four introduced and five local banana cultivars with a check variety for growth, yield and quality performances at four locations for two crop cycles. The experiment was laid out in a randomized complete block design with three replications. The results revealed significant varietal differences in plant height, days to shooting, time from planting to harvest, bunch weight, finger diameter, length and weight, yield, peel thickness, pulp-to-peel ratio, soluble solids, titratable acidity, pH, moisture and ash contents. The cultivars had generally short and thick plants. Cultivars took from 243.8 to 316.8 days to flowering while from 374.4 to 446.7 days to first harvest. The yield ranged from 43.67 to 52.46 t ha-1. Five cultivars had comparable yields to the check. The sensory results indicated that all the cultivars were generally preferred. The candidate cultivars recorded higher soluble solids, phosphorus and potassium, but lower titratable acidity than the check. The moisture and ash contents ranged from 71.53 to 76.56% and 2.50 to 3.36%, respectively. Considering the growth and yield performances as well as fruit physicochemical and sensory characteristics, ‘Lady Finger’ and ‘Dinke-1’ are recommended for production in the major banana growing areas of Ethiopia.
አህፅሮት ከኢትዮጵያ የተገኙ ሰባት የቢቬሪያ ባሲያና (Beauveria bassiana) እና ስድስት የሜታሪሂዚየም አኒሶፓሌ (Metarhizium anisopliae) የፈንገስ ዓይነቶች በቤተ ሙከራ ዉስጥ ሶስት ጊዜ በመደጋገም የፍራፍሬ ዝንብ (Bactrocera dorsalis) ትል እና ሙሽሬ ላይ የመግደል ችሎታ ተሞክሯል፡፡ የጥናቱ ዓላማ የፍራፍሬ ዝንብን በተፈጥሯዊ መንገድ ለመቆጣጠርና IPM ዘዴ ዉስጥ ማካተት ይቻል እንደሆነ ለመመልከት ነዉ፡፡ በዚሁም መሰረት ሁሉም የተሞከሩት የፈንገስ አይነቶች በ 1x108 conidia ml-1 መጠን የፍራፍሬ ዝንብ ትልና ሙሽሬን መግደል ችለዋል፡፡ ነገር ግን የመግደል አቅማቸዉ ከ 40.8% እስከ 96.0% ነበር፡፡ ከመግደል አቅማቸዉ በመነሳት S-39, 34- GM and S-46 የተባለት የሜታሪሂዚየም ዓይነቶች እና S-13 የተባለት የቢቬሪያ ዓይነቶች ከፍተኛ (81.7 to 96%) የመግደል አቅም ነበራቸው፡፡ KF-3 and PPCR-29 የተባሉት የሜታሪሂዚየም ዓይነቶች እና S-39 የቢቬሪያ ዓይነት መካከለኛ (60-80%) የመግደል አቅም ሲኖራቸዉ አንድ የሜታሪሂዚየም የፈንገስ አይነት, GF-3 ፤ እና አምስት የቢቬሪያ ዓይነቶች (9609, 9604, S-46, S-10H and DLCO-41) ደካማ የመግደል አቅም ነበራቸዉ (<60%)፡፡ የመግደል አቅማቸዉ 81.7% እስከ 96% የሆኑ ከፍተኛ ገዳይ በመባል ሲፈረጁ ይህን አቅማቸዉ በተለያዩ 6 መጠኖች (1×104, 1×105, 1×106, 1×107, 1×108, and 1×109ml-10) በተጨማሪ ተገምግሟል፡፡ በውጤቱም ከፍ ባለ መጠን (1×109 Conidia ml-1) የተሞከሩት የሜታሪሂዚየም ዝሪያ የመግደል አቅማቸዉ በትንሽ መጠን (1×104conidia ml-1) ከተሞከሩት በልጦ ታይቷል፡፡ በስድስት የተለያዩ መጠኖች በሙሽሬ ላይም የተሞከረ ሲሆን የሜታሪሂዚየም ዓይነቶች S-46 እና S-39 በከፍተኛ መጠን (1X 109) ግማሽ (50%) የገደሉ ሲሆን የቢቬሪያ ዓይነት S -13 እና የሜታሪሂዚየም ዓይነት 34-GM ከግማሽ በታች ገድለዋል፡፡ S-39 የተባለዉ የሜታሪሂዚየም ፈንገስ አይነት ከሁሉም አነስተኛ LC50 (1.2×104) ሲኖረው፤ 34-GM የተባለዉ ፈንገስ ሁለተኛወ ደረጃ ዝቅተኛ LC50 (በ1.6×104)ነበረው፡፡ በዚህም መሰረት S-39, 34-GM, S-46 የሜታሪሂዚየም ዓይነቶች እና S-13 ቢቬሪያ ፈንገስ ዓይነት የፍራፍሬ ዝንብን በተፈጥሯዊ መንገድ ለመቆጣጠር ተስፋ ሰጪ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡ Abstract The Oriental fruit fly, Bactrocera dorsalis (Diptera: Tephritidae) Hendel, has become the major pest of fruits in tropical Africa. The objective of the study was to evaluate the virulence of Ethiopian origin entomopathogenic fungal isolates of Beauveria bassiana (Balsamo-Crivelli) Vuillemin and Metarhizium anisopliae (Metchnikoff) Sorokin against the larva and pupa of the oriental fruit fly. Thirteen isolates (seven B. bassiana and six M. anisopliae) were bio-assayed in the laboratory. All the tested isolates were pathogenic to the larvae of B. dorsalis at 1x108 conidia ml-1 concentration with a mortality range from 40.8% to 96%. Isolates S-39, 34-G, and S-46 of Metarhizium and S-13 of Beauveria were categorized as highly virulent (81.7% to 96% mortality), isolate KF-3 and PPCR-29 of Metarhizium and S-39 of Beauveria moderately virulent (61.7%- 78% mortality), and isolates GF-3 of Metarhizium and 9609, 9604, S-46, S-10H and DLCO-41 of Beauveria weakly virulent (40.8-53.3% mortality). Dose-response assay was undertaken on the four highly virulent isolates at six different doses (1×104, 1×105, 1×106, 1×107, 1×108, and 1×109ml-1) on larvae of the fruit fly. The isolates varied in virulence and showed a direct relationship between mortality and concentrations. Isolate S-39 showed the least LC50 (1.2×104) followed by GM-34 (1.6×104), S-46 (1.9x104), and S-13 (1.1x105). The bio-assay on pupae of the fruit fly showed that Metharizium isolates S-46 and S-39 caused about 50% pupal mortality at the highest concentration of 1x109, while the remaining two isolates, S-13 (Beauveria) and 34-GM (Metarhizium), caused below 50% pupal mortality at all concentrations. The four tested isolates are promising bio-agents against B. dorsalis and further field trials are recommended as a component of IPM program.
አህፅሮት ይህ የመስክ ሙከራ የተሰራው በቡሬ ወረዳ እንደ ጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር 2018 የክረምት ወቅት ሲሆን የዚህ ጥናት ዓላማዎችም የበቆሎን ችግኝ አፍልቶ በማዛመት የዕድገትና የምርት አሰጣጡ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለማየት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቡሬ ወረዳ ክረምቱ ቶሎ የመውጣትና ርጥበቱ ቶሎ የመድረቅ በዚህም የተነሳ የበቆሎ ምርት መቀነስ የተለመደ እየሆነ መጥቷል። ይህ ሙከራ የተለያዩ ሁለት የችግኝ አፈላል ዘዴዎች (መደብ እና በፕላስቲክ ላይ) እንዲሁም አምስት (ከ1 እስከ 5 የእውነተኛ ቅጠል) የችግኝ የዕድገት ደረጃን እና የተለመደውን በቀጥታ መዝራት እንደ ማወዳደሪያነት በማካተት ራንደማይዝድ ኮምፕሌት ብሎክ ዲዛይን (RCBD) የሚባል ቴክኒክ በመጠቀም በሶስት ድግግሞሽ ተሰርቷል። በተለያዩ የምርት መለኪያ መንገዶች እና በኢኮኖሚያዊ አዋጭነት መሰረት በቆሎን በፕላስቲክ አፍልቶ ባለ አራት ቅጠል ሲሆን ማዛመት ከሌላው የችግኝ ዓይነት እና የዕድገት ደረጃ ብሎም በቀጥታ ከመዝራት በተሻለ የበቆሎ ምርትን ማሳደግ እንደተቻለ ተረጋግጧል፡፡ ሆኖም ሙከራው ለአንድ ዓመት ብቻ የተሰራ በመሆኑ ድጋሜ ተሰርቶ ልዩነቱን በደንብ ማረጋገጥ ቢቻል ጥሩ ነው። Abstract The field experiment was conducted during the rainy season of 2018 in the Burie district to evaluate the effect of types and growth stages of seedlings on yield and yield-related traits of transplanted maize (Zea mays L.). In the District, terminal moisture stress and grain yield loss become the common challenges in maize production. The experiment was conducted in factorial combinations of two types of seedlings (bare-rooted and polybagged) and five levels of seedling’s growth stages (seedlings of 1, 2, 3, 4 and 5 true leaf/ves) pulse one control (direct-seeded). The treatments were laid down in RCBD with three replications. Data on yield and yield-related parameters were collected following standard procedures and subjected to analysis of variance using SAS software; and mean separation for significant treatments was done by LSD. Both main effects affected the number of grains cob-1, grain and stover yield highly significantly. Types of seedlings significantly affected the number of cobs plant-1, cob length, the number of grains row-1, and biomass yield. The number of cobs plant-1, cob length, number of grains row-1and biomass yield was also highly significantly affected by seedlings growth stages. The interaction effect was highly significant on a number of cobs plant-1, grain and stover yield and very highly significant on harvest index. The highest (10.7t ha-1) grain yield of maize was found from the transplantation of polybagged seedlings at four-leaf stages. This treatment combination also gave the highest net benefit with an acceptable range of marginal rate of return. Therefore, transplanting of polybagged seedlings at four true leaf stages is economically feasible and can be recommended tentatively for Burie District and similar agro-ecologies. However, to come up with a concrete recommendation, it is advised to repeat the study in similar agro-ecologies of maize production.
አህፅሮት እንሰት አመቱን ሙሉ አረንጓዴ የሚሆንና ድርቅን የሚቋቋም ዕፅዋት ሲሆን ለምግብነት፣ ለመኖ፣ ለቃጫ፣ ለማገዶ፣ ለመድሀኒትነት እና ለተለያዩ ባህላዊ ክንውኖች ይጠቅማል፡፡ የጌዶኦ ዞን እንሰት አመራረት ከሰው ልጆችና ከሌሎች ህይወት ካላቸው ፍጥረቶች ጋር በቁርኝት የሚገኝ ነው፡፡ አብዛኛው የእንሰት ምርምር ስራዎች በደጋማና ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች በማተኮር የሚሰሩ ሲሆን እነዚህም አካባቢዎች በእንሰት ምርታማነት የሚታወቁ ናቸው፡፡ ይህም ሁኔታ ዝቅተኛ ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች ላይ የእንሰትን ጥቅምና አገልግሎት እንዲያንስ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም የዚህ የምርምር ዋና አላማ ሁሉንም ስነ-ምህዳር ባገናዘበና ባካተተ ሁኔታ የእንስሳት አመራረትንና አዘገጃጀት በጌዲኦ ያለውን ገጽታ ለማሳየት የተደረገ ጥናት ነው፡፡ ይህንንም ተግባራው ለማድረግ ሶስት ስነ-ምህዳርን የሚወክሉ ሰባት ቀበሌዎች ከሶስት ወረዳዎች ተመርጠዋል፡፡ በመቀጠልም ስለ እንሰት ከፍተኛ ግንዛቤ ያላቸውንና ፍቃደኛ የሆኑ የማህበረሰቡን አካላት ጋር ዘርዘር ባለ ሁኔታ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡ ለውይይት መነሻነትም መጠይቅ ተዘጋጅቷል፡፡ በመጠይቁ ከአምራቾች አስተሳሰብና ትግበራ አንጻር የእንሰት የስነ-ምህዳር ፍላጎት፣ የአረባብ ሁኔታ፣ የአፈር አጠባበቅ፣ የአተካከል ሁኔታ፣ የበሽታና የተባይ ሁኔታ፣ የምርት አሰባሰብ፣ እንዲሁም የምርት አዘገጃጀትና አቀማመጥ ሁኔታ መረጃ በ230 መጠይቅ በመጠቀም ተሰብስቧል፡፡ ከመረጃውም ብዙዎቹ የእርሻ ሥራዎች በባህላዊ መንገድ እንደሚሰሩ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ተጨማሪም አንዳንድ በዘር የማራባት ዘዴ ዓይነት ወሳኝ የእርሻ ተግባራት የተዘነጉበት ሁኔታም እንዳለ ለመረዳት ተችሏል፡፡ Abstract Enset is a perennial, drought-tolerant, banana-like plant that used for food, fodder, fiber production, fuel, traditional medicine, and for other different cultural practices. The enset production system of Gedeo expresses complex interrelationships between humans and biological diversity. The majority of research studies focused on higher altitudes, where enset production was established successfully for a long time. However, enset can grow in a wide range of environments including lower altitudes, where the potential use of the crop might be further exploited. Hence, the objective of this research was to provide information on on-farm management and processing of enset across the different agroecology of Gedeo Zone, Southern Ethiopia. From the three agroecological representative woredas, a total of seven sample kebeles were selected. Detailed information from volunteer key informants on the crop agroecological preferences, crop calendar, propagation techniques, planting methods, soil management, disease, and pest management, harvesting, processing, and storage methods were collected. This information was organized and developed into a structured questionnaire. A total of 230 randomly selected farmer households were included in the data. In the study area, enset crop-management and processing activities performed using traditional methods. Some alternative techniques and approaches, such as the seed propagation method overlooked.
አህፅሮት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ ዓይነት ምጥን ማዳበርያዎች፣ ዳፕ እና ዩርያን በመተካት ወደ ሃገራችን ለሙከራ የገቡት በቅርቡ ነው፤ NPSZn ምጥን ማዳበርያም አንዱ ነው፡፡ የተለያየ መጠን NPSZn (0፣ 50፣ 100፣ 150፣ 200፣ 250፣ 300 ኪ.ግ በሄክታር) እና የተለመደው ዩርያና ዳፕ ማዳበርያ እንደ መወዳደርያነት በማካታት በራንደማይዝድ ኮምፕሊት ብሎክ ዲዛይን (RCBD) በሶስት ድግግሞሽ በ2009ዓ.ም እና 2010ዓ.ም በትግራይ በኦፍላ እና እምባ አላጀ ወረዳዎች ተሞክሯል፡፡ የቅድመ ተከላ የአፈር ናሙና እንደሚያመለክተው የናይትሮጅን መጠን በአብዛኛው የምርምር ሳይቶች ዝቅተኛ ሲሆን የፎስፎረስ መጠን ደግሞ መካከለኛ ነበር፡፡ በተለያየ የምርት መለኪያ መንገዶች እና በኢኮኖሚያዊ አዋጭነት መሰረት 200ኪ.ግ NPSZn ምጥን ማዳበርያ ከ62 ኪ.ግ ዩርያ በኦፍላ እንዲሁም 100ኪ.ግ NPSZn ምጥን ማዳበርያ ከ100ኪ.ግ ዩርያ በእምባ አላጀ ከሌሎች የማዳበርያ መጠኖች በተሻለ በስንዴ ምርት ላይ የተሻሉ እንደሆኑ ተረጋግጧል፡፡ Abstract A field experiment was carried out in 2017 and 2018 main cropping seasons in Ofla and Emba Alaje Woredas in Tigray Regional State, Ethiopia. The experiment has seven levels of NPSZn (0, 50, 100, 150, 200, 250, 300, kg ha-1) adjusted for N from urea to the recommended N level (64 kg N ha-1) and the recommended P fertilizers (46 kg P2O5 ha-1). The treatments were also arranged in a randomized complete block design (RCBD) with three replications and executed on two farmers' fields. Soil samples were collected before planting and analyzed for selected physicochemical properties. As a result, the application of different rates of NPSZn blended fertilizer significantly influenced the yield and yield components of wheat at both sites. At Ofla, the highest grain and straw yields were obtained from plots that received 200 kg NPSZn ha-1 . At Emba Alaje, the highest grain and straw yields were harvested from the application of 200 kg NPSZn ha-1 and 100 kg NPSZn ha-1, respectively. Application of Zn in the blended fertilizer had no significant effect on grain Zn concentration of bread wheat at both sites. Partial budget analysis revealed that the optimum marginal rate of return was 22.25ETB and 16.06ETB at Emba Alaje and Ofla, respectively. Both biological and economic analysis showed that applications of 200kg NPSZn with 28.6 kg N (62 kg urea) at Ofla and 100 kg NPSZn with 46 kg N (100 kg urea) at Emba Alaje were optimum for wheat production and these rates could be recommended for areas where the rainfall distribution and soil types are similar with the study locations. Further study should be done on the effects of NPSZn on grain quality and a single nutrient-based experiment should be carried out to evaluate the effect of each nutrient in the blended fertilizer for crop production.
አህፅሮት በኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች አካባቢ በተደጋጋሚ ድርቅ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ ይህ ደግሞ ለአየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያታዊ ከሚሆኑት ነገሮች ዉስጥ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለሁለት አስርት ዓመታት በቦረና አርብቶ አደሮች አካባቢ ከነበሩት ስጋቶች ከፍተኛዉ የድርቅ ሁኔታ ስለነበር በኢኮኖሚ እና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት ከሚስተዋሉት ከባድ የሆነ የድርቅ ሁኔታ በ2010ዓ.ም በቦረና አርብቶ አደሮች ላይ ደርሷል፡፡ በዚሁ ምክንያት በርካታ የሆኑ ከብቶቻቸዉ አልቀውባቸዋል፤ አገሪቱንም ለከፍተኛ ወጪ ዳርጓታል፡፡ ከዚህ በፊት የአየር ጠባይ ለዉጥ ሁኔታዎችን ለመቋቋም አስመልክቶ ብዙ ጥናቶች ቢደረጉም የአርብቶ አደሮች አገር በቀል የአየር ጠባይ ለዉጥን የመቋቋምያ ዕዉቀታቸዉ፤ በአከ ባቢ ሁኔታ፣ በህብረተሰብ፣ በኢኮኖሚ እና በተቋማዊ ሁኔታ ከብቶችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላኛዉ ቦታ በማንቀሳቀስ መጠበቅ እንዲሁም ብዙ ከብቶችን ከፋፍሎ በመጠበቅ ነው፡፡ ይህንኑ ሁኔታ በማገናዘብ ብዙ ጥናቶች ስላልተሰሩ ይኸ ጥናት እንዲሰራ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ዓላማ በደቡብ ኢትዮጵያ በቦረና ዞን የአርብቶ አደሮች አገር በቀል ዕዉቀት ፋይዳዉን መዳሰስ ነዉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሚታዬዉ የድርቅ ሁኔታ እና የአየር ጠባይ ለዉጥ ለመቋቋም የሚያስችል የአካባቢዉ ህብረተሰብ ዕዉቀት፤ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዙሪያ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በዚህ ጥናት አካባቢዉን መወከል በሚችል ሁኔታ 352 አባወራዎች ተካቷል፡፡ የቡድን ውይይት እና ከጥናቱ ሁኔታ ጋር ልምድ ያላቸዉ አባወራዎች ተዳርሷል፡፡ ጥናቱ ታስቦበት የተሰራ ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩ የጥናት ዘዴዎችን በመጠቀም ጥራት እና ብዛት ያላቸዉ መረጃዎችን በመሰባሰብ ሳይንሳዊ በሆነ አኳን የጥናቱ ዉጤት ተተንትኗል፡፡ በቦረና አርብቶአደሮች አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የአዬር ጠባይ ለዉጥ ከመኖሩ የተነሳ ከብቶችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላኛዉ ቦታ በማንቀሳቀስ እና ከፋፍሎ በመጠበቅ የድርቅና የአዬር ጠባይ ለዉጥ ሁኔታ መቋቋም ይኖርባቸዋል፣ አገር በቀል ዕዉቀታቸዉን ስራ ላይ እንዲያዉሉ ይመከራል፡፡ Abstract There is no doubt that the drought frequency, which is attributed to climate change and variability among other causes, is increasing in both severity and length in all pastoral areas of Ethiopia. It has been threatening pastoral societies of the Borana with increasing substantial economic losses and humanitarian suffering in the last two decades. We have a very recent shocking memory of the 2017 drought in the most pastoral areas of Ethiopia including the Borana zone that resulted in the deaths of thousands of livestock that turned thousands of people to be dependent on humanitarian aid, and then it forced the country to spend $billions on relief. Though numerous researches have been done on climate change adaptation practices, little study has been conducted concerning the role of indigenous knowledge of pastoral communities in climate change adaptation in specific ecological, social, economic, and institutional contexts and the current range of mobility, and stock diversification. In this case, our study aimed at investigating the role of Borana pastoralists’ indigenous knowledge in drought risk reduction in southern Ethiopia. Multiple data sources, including socioeconomic interviews with 352 household heads, focus group discussions, and key informant interviews with pastoralists were used to capture various aspects of the current drought and drought adaptation and coping practices. The study utilizes multiple research designs and multistage random, purposive sampling methods. The qualitative and quantitative data were analyzed and the findings indicated that mobility and stock diversity remain the most common method of coping with drought and is recommended that supporting the traditional coping mechanisms and promoting viable programs that support livestock and livelihoods due to the variability of their environment.
አህፅሮት ይህ ምርምር የተካሄደው በጨንቻ (ኢትዮጵያ) የበቀሉ ሦስት የአፕል ዝርያዎች ከተመረቱ በ3 ሳምንታት ክምችት ጊዜ የሚያሳዩትን ለውጦች ለማወቅ ነው። ሁሉም የተለኩ የጥራት አመላካቾች በሦስቱ ዝርያዎች፣ በብስለት ደረጃቸውና በማሸጊያ (መያዣ) ዓይነቶች ትርጉም ባለው ደረጃ ልዩነት አሳይቷል። በብዙ አምራቾች ገበያ ለመሻማት የሚደረገውን ለመወከል ከትክክለኛው የመሰብሰቢያ ጊዜው በ2 ሳምንታት ቀድመው የተለቀሙት ናሙናዎች ከፍ ያለ ጠጣርነት (ጥንካሬ) አስመዝግበዋል። እንደዚሁም አነስተኛ ጥቅል ሟሚ ጥጥሮችም (total soluble solids) ለነዚሁ ቀድመው ለተለቀሙ ናሙናዎች (በዝርያ ሳይለይ) ተመዝግቧል። ጠጣርነቱ (ጥንካሬው) በክምችቱ ጊዜ እየቀነሰ ሲሄድ ጥቅል ሟሚ ጥጥሮቹ (በብዛት ስኳር) ግን መጠናቸው እየጨመረ መሄዱ በተወሰነ ደረጃ የተስተዋለ ሲሆን ይህም የአፕል ፍሬዎቹ ለመብል ተፈላጊነታቸው (ልስላሴና ጥፍጥናቸው) እየጨመረ መምጣቱን ያሳይ ይሆናል። ይሁንና በእሼትነታቸው የሚበሉ እንደ አፕል ያሉ ፍራፍሬዎች መሰብሰብና ለገበያ መቅረብ ያለባቸው እድገታቸውን ጨርሰው በትክክለኛው የብስለት ጊዜያቸው እንደሆነ እና በዚህ መንገድም የተሻለ ዋጋ እንደሚያወጡ ለአምራቾቹ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠናዎችና የኤክስቴንሽን ሥራዎች እንደሚያስፈልጋቸው ማስገንዘብ ተገቢ ነው። Abstract This research was conducted to understand changes of physicochemical properties of fruits of three apple cultivars as influenced by the stage of maturity and packaging types over a storage period of three weeks. The research was designed to replicate practices by the producers and along the value chains and to assess the fruit quality under the conditions of the major markets in the region. All the measured physicochemical parameters significantly varied with the cultivars, maturity stage at harvest, and packaging types. Higher firmness was recorded for the samples harvested about two weeks before the optimal maturity, usually practiced by a significant number of producers to gain market advantage. Lower total soluble solids corresponded to the early harvested samples regardless of cultivars and packaging types. The firmness was observed decreasing over the storage periods whereas the total soluble solids increased, which is associated with improving sensorial quality for the early harvested cultivars as the soluble solids are mainly sugars. The early harvesting resulted in fruits of inferior desirability including extreme hardness, firmness, and low total soluble solids that may have high sourness and less sweet taste. Awareness creation for the producers on the quality and advantages of harvesting their produces at optimal maturity and practicing good postharvest management is required.
አህፅሮት ድንችን በባህላዊ መንገድ በመጠን የመለየት ስራ ብዙ ሰዓትና የሰው ጉልበት የሚፈልግ በጣም አድካሚና አነስተኛ ውጤት የሚያስገኝ ስራ ነው። ስለሆነም ድንችን ወደ ተለያየ መጠን የሚለይ በሞተር ኃይል የሚሰራ ማሽን ፍተሻ እና የመገምገም ስራ ተሰርቷል። የመለያ ማሽኑ በተለያየ መጠን የሚለየውን ድንች ማስገቢያ፣መለያ ሲሊንደር፣ኃይል ማስተላለፊያ ዘንግና መቀበያ አሉት። ሙከራው በተለያየ ጡዘት (10፣15 እና 20 ጡዘት በደቂቃ)፣ ዘዌ (5፣10 እና 15 ዲግሪ) እና በተለያየ የድንች አጨማመር በደቂቃ (20፣ 30 እና 40ኪ.ግ) በስፕሊት ስፕሊት ፕሎት የሙከራ ዲዛይን (split split plot design)ተከናውኗል። የማሽኑን የድንች የመለየት አቅም፣ የመለየት ስርዓት ውጤታማነት፣የነዳጅ ፍጆታ እና መካኒካዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት የመገምገም ስራ ተከናውኗል። የፍተሻ ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት የማሽኑ የመለየት አቅም እና የነዳጅ ፍጆታው የመለያ ሲሊንደሩ ፍጥነት እና የሚለየው የድንች መጠን ሲጨምር አብሮ የሚጨምር ሲሆን የድንች ሜካኒካዊ ጉዳት እና የመለየት ስርዓት ውጤታማነት ደግሞ የዘዌ መጠን ሲጨምር እየቀነሰ ይሔዳል። ከፍተኛው የማሽኑ የመለየት ስርዓት ውጤታማነት የተገኘው ማሽኑ በ15 ጡዘት በደቂቃ እና በ5 ዲግሪ ዘዌ፤ 20 እና 30 ኪ.ግ. በደቂቃ ድንችን በተለያየ ጊዜ በመጨመር በሚለይበት ጊዜ 97.57 እና 97.67% በቅደም ተከተል ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ የድንች መለያ ማሽን የኢኮኖሚ አዋጭነቱ ተጠንቶ በሀገር ውስጥ አምራቾች ተባዝቶ ለተጠቃሚዎች ቢቅርብ የድንች አምራቾችና በምርት እሴት ሰንሰለት ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን ውጤታማነትን ያሳድጋል። Abstract Traditional methods of grading potato tubers require high labor-hour, cause fatigue to workers, and have low output. Hence, an engine-driven machine capable of grading potato tubers into different size classes was evaluated. The grader prototype consisted of a feeding table, grading cylinder, and catchment tray. Grading capacity, grading system efficiency, mechanical damage, and fuel consumption were used to determine the performance of the machine. Split-split-plot experimental design where grading cylinder speeds (10, 15, 20 rpm) were the main plots, angle of inclinations (5, 10, and 15°) as sub-plots, and feeding rates (20, 30, 40 Kg.min-1)as sub-sub-plots with three replications were used. The results indicated that grading capacity and fuel consumption increased with increasing cylinder speed and feed rate while percentage mechanical damage and grading system efficiency decreased with increasing angle of inclination. The maximum grading system efficiency of 97.57% and 97.67 % was observed when the machine was operated at speed of 15rpm, angle of inclination of 5°, and feed rate of 20 and 30 kg.min-1, respectively. From the performance indices, it can be concluded that the performance of the machine is very much acceptable with a high prospect for extending the technology for small and medium-scale farmers and potato whole sellers along the value chain.
አህፅሮት ይህ ምርምር ጥናት ሥራ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በተሳትፏዊ ተከላ ርቀት ለተሻላ ሽንኩርት ምርት በአነስተኛ መስኖ በሚል በአርባምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል የተሰራ ነዉ፡፡ ሙከራዉ የተካሄደዉ በአራት ተከላ ርቀት ማለትም በ8 ሳ.ሜ፣ በ10 ሳ.ሜ፣ በ12 ሳ.ሜ እና አርሶ አደሩ በለመደዉ ወይም እራሱ በሚተክለዉ ነዉ፡፡ የሌሎች ግብአቶች አሰጣጥ ማለትም ማደበሪያ፣ ዩሪያ፣ ዉሃ፣ ኬሚካልና አረም ቁጥጥር ሥራ ለሁሉም ተከላ ርቀት ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡ ከአራቱም ሽንኩርት ተከላ ርቀቶች የተሻለ ምርት ዉጤት የተገኘዉ በ10 ሳ.ሜ (17.178 ቶን በሄክታር) እና 12 ሳ.ሜ (17.740 ቶን በሄክታር) ነዉ፡፡ በዚህ ጥናት አርሶ አደር በእራሱ ልምድ በአማካይ ተከላ ርቀት 7.3 ሳ.ሜ የተገኘዉ ምርት ዝቅተኛ ዉጤት (11.464 ቶን በሄክታር) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እንደ ኮምፕዩተር ፕሮግራም ትንተና ከአርሶ አደር ተከላ ርቀት ዉጭ፤ በሌሎቹ ተከላ ርቀቶች ምንም ዓይነት ልዩነት አልታየም፡፡ ምንም እንኳን የተገኘዉ ምርት ዉጤት በአማካይ አነስተኛ ቢሆንም፤ በወቅታዊ ገበያ አንፃር በአንድ ኪሎ ግራም 34 ብርና በሄክታር 532,831ብር በመሸጥ አርሶ አደሩ ከሌሎቹ ጊዜያት የተሻለ ገቢ ያገኘበት ጥናት ነዉ፡፡ ይህ ዋጋ ጭማሬ የታየዉ፣ በወቅቱ ከተመረተዉ አነስተኛ ምርት መጠን መሆኑ ታዉቋል፡፡ ከዚህ ጥናት መነሻ፤ ተሳትፏዊ አነስተኛ መስኖ ሥራ ላልተጠበቀዉ አየር ንብረት ለዉጥም ሆነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለዉ ታይቷል፡፡ ስለዚህ በተሳትፏዊ አነስተኛ መስኖ ሥራ ሽንኩርት በጥሩ ሁኔታ በተዘጋጀ ማሳ በ10 ሳ.ሜ ተከላ ርቀት ቢተከል፤ ምረትና ምርታማነትን ሳይቀንስ አርሶ አደሩን ይበልጥ ዉጠታማ ያደርገዋል፡፡ Abstract This study was conducted for two consecutive years to find optimum onion spacing under full irrigation, which allows the maximum yield of onion at Kencho kebele of Uba debretsehay woreda Gofa Zone Southern, Ethiopia through the support of the Participatory Small-scale Irrigation Development Program(PASID II). The experiment has four levels of onion planting spacing (8cm, 10cm, 12cm, and Farmer's practice or planting with own practice), laid down in Randomized Completed Block Design (RCBD) with four Replications. The same amount of irrigation water (416.56mm) which is 100%ETc was applied for all treatments in the five-day intervals during the study. There was no significant difference among treatment spacing 8cm,10cm, and 12cm on the total yield of onion (16.304 t/ha,17.178 t/ha, and 17.740 t/ha), respectively. The only statistical difference was observed between the three treatments and farmer practice which is 7.3cm (11.464t/ha) on average spacing. Accordingly, farmers’ (FREG) were very profitable from the study in both years. Of course, the yield obtained from the study was very low as compared to the potential yield of Red Creole variety in Ethiopia. As a result, farmers were earned a seasonal income of 34ETB/kg which was very costly, and 532,831ETB/ha on average from seasonal production. This implies that low production potential, but makes high profitable for the farmers during the season. So the PASIDP has vital economic values on the livelihood of farmers and even good training for neighborhood farmers. Therefore it was recommended that application appropriate onion spacing of 10cm with a properly managed field irrigation system makes it highly profitable with marketable yield under full irrigation (100%ETc).
አህፅሮት የቡና ምርትና ምርታማነት ከሚቀንሱ የቡና በሽታዎች መካከል የቡና ግንድ አድርቅ በሽታ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ይህን በሽታ በተለያየ መጠን የመቌቌም ችሎታ ያላቸው የቡና ጀኖታይፖች በመጠቀም የዘር ውርስ ሂደቱን ወይም የመቌቌም ስነባህሪውን በማጥናት በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል የመሻሻያ መንገዶችን ለመቀየስ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የምርምር ስራው ተካሂዷል፡፡ ይህ ጥናት ሰምንት የእናት ቡና ጀኖታይፖችንና ከነዚህ የተገኙ 28 የመጀመሪያ ድቃዮችን እንዲሁም አንድ በበሽታው የሚጠቃ ማነፃፀሪያ በመጠቀም ተካሂዷል፡፡ በ2007/8 ዓ.ም በጥናቱ ላይ የተካተቱት የቡና ጀኖታይፖች ለበሽታው ያላቸውን አቌም በጅማ ግብርና ምርምር የእፅዋት ጥበቃ ግሪን ሃውስና ላብራቶሪ ውስጥ በመከተብ ተገምግመዋል፡፡ በሽታውን በተከተቡ ችግኞች ላይ የደረቁ የቡና ችግኖች ብዛት በፐርሰንት፤ የበሽታ ምልክት የሚታይበት የጊዜ ርዝመት፤በበሽታው የረገፉና ወደ ቢጫነት የተለወጡ የቅጠል ብዛት መረጃዎችን በመውሰድ የተለያዩ ስታስቲካዊ ዘዴዎችንና ፓኬጆችን በመጠቀም የመረጃ ትንተና ተደርጓል፡፡ በዚህ ጥናት መሰረት የደረቁ ችግኖች ብዛት በመቀነስ፤ የበሽታ ምልክት የሚታይበት የጊዜ ርዝመት በማሳጠርና በበሽታው የሚረገፉ የቅጠል ብዛት በመቀነስ ረገድ ያላቸው የሃይለድቅል መጠን በሽታውን ሊቌቌም በሚየስችል ሁኔታ ወይም በሚፈለገው ደረጃ መሻሻል አላሳየም፡፡ እናት ቡናዎች P2 (971)፤ P7 (974)፤ P8 (370 እና P5(79233) በሽታ የመቌቌም ባህሪያቸውን ለድቃዮቻቸው በማስተላለፍ ከፍተኛ የሆነ ድርሻ እንዳላቸው ታውቌል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ P7 x P8 (974 x 370) እና P4 x P8 (8136 x 370) ድቃዮች በጥሩ ሁኔታ በሽታውን የመቌቌም አቅም አሳይተዋል፡፡ በተጨማሪም ይህን በሽታ የሚቌቌሙ የቡና ጀኖታይፖች የመቌቌም ስነባህሪያቸው እስከ 68.61% የመሻሻልና የመተላለፍ አቅም ከፍተኛ መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ጥናት መሰረት የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን የመቌቌም ስነባህሪን በመረጣና ከድቀላ በኋላ የዘርሀረግን መሰረት አድርጎ መረጣ በማካሄድ ማሻሻል እንደሚቻል ታውቌል፡፡ Abstract Combining ability, heterosis, and heritability studies can provide valuable information for designing appropriate breeding programs for resistance to coffee wilt disease (CWD) caused by Gibberella xylarioides. The objective of this study was conducted to determine heterosis, combining ability, and heritability for resistance to CWD using an eight-parent half diallel cross (eight parents and 28 F1 hybrids). A susceptible control was used as a reference. All entities were artificially inoculated by the pathogen in a greenhouse and evaluated for CWD at Jimma Agricultural Research Center (JARC), Ethiopia in 2015/16. The reactions of inoculated genotypes were measured as a percent of wilted seedling, incubation period, and a number of yellow and defoliated leaves. Combined analysis of variance showed significant differences among genotypes for the characters measured. Better-parent heterosis (BPH) and mid-parent heterosis (MPH) for percent of wilted seedlings and the number of defoliated leaves showed negligible heterosis in a desirable direction. However, considerable MPH was noticed for an extended incubation period. Both additive and non-additive gene actions were involved in controlling the inheritance of CWD resistance and incubation period; the additive gene effects being predominant. Parents P2 (971), P7 (974), P8 (370), and P5 (79233) showed highly significant negative general combining ability (gca) effects and were found to be good general combiners for resistance to CWD. Moreover, specific combining ability (sca) effects of hybrids P7 x P8 (974 x 370) and P4 x P8 (8136 x 370) revealed that they are good combinations for resistance (low mean wilted seedlings percentage) and incubation period. Percent wilted seedlings showed high broad (88.27%) and narrow (75.41%) sense heritability coupled with 68.61% genetic advance. Generally, both pure line selection and pedigree selection after hybridization could be an effective resistance breeding approach.
አህፅሮት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ህዝብ ለመመገብ በአንድ የእርሻ ማሳ ላይ ምርታማነትን ማሳደግ በጣም አስፈለጊ ነው፡፡ ስለሆነም ሰብልን አሰባጥሮ መዝራት ምርትን ለማሳደግ ተስፋ ሰጪ ሥርዓት ተደርጎ ይወሰዳል በተጨማሪም ምርታማነትን እና የመሬት አጠቃቀምን ውጤታማ ያደርጋል፡፡ የስንዴ እና ምስር የተለያዩ የሰብል ስብጥር በስንዴ እና በምስር ምርታማነት እና የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት በሁለት የእርሻ አስተራረስ ዘዴ ለመገምገም በምንጃር ወረዳ እ.ኤ.አ. ከ 2015-2017 ባለው የሰብል ምርት ወቅት የመስክ ጥናት ተካሂዷል፡፡ ምርምሩ የተካሄደዉ እስፕሊት ፕሎት በተባለ ዲዘይን ሲሆን እያንዳንዱ ትሪትመንት ሶስት ጊዜ ተደጋግሟል፡፡ ትሪትመንቶቹ ያካተቱት ሁለት የአስተራረስ ዘዴ (ባህላዊ እና ዝቅተኛ) በዋና ፕሎት ላይ ሲዉሉ አምስት የስንዴ እና ምስር ስብጥር አዘራር ዘዴ(1፡0፤1፡1፤2፡1፤1፡2 እና 0፡1) ደግሞ በንዑስ ፕሎት ላይ በማድረግ ነዉ፡፡ የሙከራዉ ዉጤት እንዳሳየዉ በስንዴ እና ምስር የእድገት መለኪያዎች ላይ ጉልህ ተፅኖ አልነበረዉም፡፡ የአስተራረስ ዘዴዎችም በስንዴ ምርታማነት ላይ የጎላ ተፅኖ አልነበረዉም ነገር ግን በምስር ምርታማነት ላይ የጎላ ተፅኖ ነበረዉ፡፡ ከፍተኛ የምስር ምርት (1546 ኪ.ግ/ሄ.ክ) የተገኘዉ ከዝቅተኛ የአስተራረስ ዘዴ ሲነፃፀር የባሕላዊ አስተራረስ ዘዴ የተሸለ ምርት አስገኝቷል፡፡ በስብጥር አዘራር ዘዴ በሁለቱም ሰብሎች ላይ የጎላ ተፅኖ ነበረዉ፡፡ ከፍተኛ የስንዴ ምርት (2932 እና 2982 ኪ.ግ/ሄ.ር) የተገኘዉ ስንዴ ብቻውን ሲዘራ (1፡0) እና 2፡1 ስንዴ እና ምስር ስብጥር ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ አሰባጥሮ መዝራት የምስር ምርት እንደሚቀንሰው ጥናቶ ያሳያል፡፡ ከስብጥር አዘራር ዘዴ መካከል 2፡1 ስንዴ-ምስር ስብጥር ከፍተኛ የመሬት አጠቃቀም፤የመሬትና የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም የገንዘብ ጥቅም አስገኝቷል፡፡ ስለሆነም 2፡1 ስንዴ-ምስር ስብጥር ለስንዴ እና ምስር በስብጥር የማምረት ዘዴ ምቹ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ Abstract To feed the ever-increasing population, increase productivity per unit area is one of the most attractive strategies. Intercropping is considered a promising system for increasing crop productivity and land-use efficiency. A field study was conducted to evaluate the effect of different crop combinations of wheat-lentil on the productivity of wheat (Triticum aestivum L.) and lentil (Lens culinaris) and land-use efficiency under two tillage practices in Minjar district during 2015-2017 cropping seasons. The experiment was carried out using split-plot design with three replications. The treatments consisted of two tillage practices (conventional and minimum tillage) assigned as the main plot and five wheat-lentil intercropping combinations (1:0, 1:1, 2:1, 1:2 and 0:1) assigned as the subplot. The tillage practices and intercropping had a significant effect on the growth parameters of wheat and lentil. Minimum tillage increased growth parameters for wheat, but reduced growth parameters for lentil. The yield of wheat was non-significantly affected by tillage practices, but the yield of lentils was significantly affected by tillage systems. A higher yield of lentil (1546 kgha-1) was obtained in conventional tillage as compared to minimum tillage practices. Intercropping combination had a significant effect on both the growth and yield parameters of both crops. The highest yield of wheat (2932 and 2982 kgha-1) was recorded in sole wheat (1:0) and 2:1 wheat-lentil combination, while the highest yield of lentil (1575 kgha-1) was obtained in sole lentil (0:1). Among intercropping combinations, 2:1 wheat-lentil gave the highest LER, ATER, and MAI values. Therefore, 2:1 wheat-lentil intercropping combinations were found suitable for higher productivity and production of component crops, and the intercropping system of wheat-lentil in any of the combinations found to be more profitable and productive compared to sole wheat and lentil.
አህፅሮት ይህ ጥናት የተካሄደው በ2011 ዓ.ም በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ነበር፡፡ የጥናቱ ዋና ዓላማ የበቆሎ ገፈራን ከተለያዩ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች ማለትም ፋግሎ፣ ፉርሽካ፣ ጥጥ ፍሬ፣ ሞላሰስ እና ጨውን በማዋሀድ በታላቢ የወተት ላሞች የወተት ምርት እና ተዋፅዖዎች (ለምሳሌ የቅባት፣ የገንቢ እና የማዕድናት ንጥረ-ነገሮች) ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ማጥናት ነበር፡፡ ለዚህ ሙከራም በቆሎን በመዝራትና በእሸት ደረጃው በማጭድ፡ በቆሎውን እና አገዳውን በመለያየት በቆሎውን በፀሀይ በማድረቅ እና ርጥብ የበቆሎ አገዳውን በመፍጭት (ከ5-10 ሳ.ሜ) ሙከራው ተጀመረ፡፡ አንድ እጅ የተፈጨ የበቆሎ አገዳን (ከ5-10 ሳ.ሜ) ከሶስት እጅ ሞላሰስ እና ውሃ ጋር በማዋሀድ ለተከታታይ 45 ቀናት በጉድጓድ በመቅበር የበቆሎ አገዳ ገፈራ ተዘጋጀ፡፡ ከዚህም በመቀጠል የተለያየ መጠን ያለው የበቆሎ አገዳ ገፈራ እና ኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች በማዋሀድ ውህድ የእንስሳት መኖ ተዘጋጅቷል፡፡ ለዚህ ምርምር 1ኛ፡ የተፈጥሮ ድርቆሽ እና የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች(0.5 ኪ.ግ ለ1 ሊትር ወተት ምርት) ` 2ኛ፡- 70 እጅ የበቆሎ አገዳ ገፈራን ከ30 እጅ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች 3ኛ፡ 60 እጅ የበቆሎ አገዳ ገፈራን ከ40 እጅ ከኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች እና 4ኛ፡ 50 እጅ የበቆሎ አገዳ ገፈራን ከ50 እጅ ከኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች ጋር በማዋሀድ ለታላቢ ላሞች ለተከታታይ አንድ መቶ (100) ቀናት በመመገብ በወተት ምርት እና ተዋፅዖዎች ላይ ያለውን ተፅዕኖ ማየት የተቻለ ሲሆን አራተኛው አማራጭ (50 እጅ የበቆሎ አገዳ ገፈራን ከ50 እጅ ከኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች ጋር በማዋሀድ ለታላቢ ላሞች መመገብ) የተሻለ የወተት ምርት ማግኘት የተቻለ ሲሆን በሶስቱም የአመጋገብ አማራጮች ላይ የተጋነነ የወተት ተዋፅዖዎች ልዩነት አልታየም፡፡ Abstract This study was conducted at Holetta agricultural research center, Ethiopia with the major objectives to evaluate the effect of silage made from late maturing dual purpose maize crop on intake digestibility, milk yield and composition of dairy cows. A total of eight mid lactating F1 (Boran X Friesian) dairy cows with similar milk yield (9.1 ± 0.91 kg/d) but differing in parity (ranges one to four) were selected and randomly assigned into one of the four dietary treatments (T1=Natural pasture hay ad libitum + 0.5 kg concentrate mixture (CM) per liter of milk production; T2=TMR-1 (70% MSS: 30% CM) ;T3=TMR -2(60% MSS: 40% CM) and T4=TMR-3 (50% MSS: 50% CM) in a double 4X4 Latin square design. The cows fed T1 and T4 diet had similar DM, OM and NDF intakes (P>0.05) which is significantly higher over cows receiving the remaining treatments (P 0.05) on milk composition. Feeding maize stover silage harvested at late maturity to crossbred cows resulted better daily milk yield; however, further study is required on the economics aspect before the diet is recommended for wider use under field conditions in Ethiopia.
አህፅሮት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛና ከፍተኛ የሆነ የቡና ብዝሃ-ሕይወት እንደሚገኝበት ይታወቃል፡፡ ጥራት የቡናን ዋጋ እንዲሁም በቡናው ምርት ላይ ያለውን ጠቀሜታ ይወስናል፡፡ በቤንችማጂና ሸካ ዞን አካባቢ ያለውን የቡና ጥራት ጣዕም ለመገምገምና ከአፈርና ከአካባቢያዊ የአየር ሁኔታ ጋር ያለውን ተዛምዶ ለማጥናት ይህ ሙከራ ተከናውኗል፡፡ ጥናቱ የተከናወነው ነስትድ (Nested) በተባለ ዲዛይን በሶስት ድግግሞሽ ነበር፡፡ ቀበሌዎቹ በወረዳ ውስጥ ነስትድ (Nested) ሆነው የተለያዩ ሶስት የቡና ማሳዎች በአንድ ቀበሌ ውስጥ ለድግግሞሽ ውለዋል፡፡ በአጠቃላይ 162 የቡና ናሙናዎች ተሰብስበው በጅማ የግብርና ምርምር ማዕከል የቡና ጥራት ባለሙያዎች የጥሬና የጣዕም ትንተና ተከናውኗል፡፡ በአብዛኛው የቡናው የጥሬና የጣዕም ባህሪያት በናሙናዎቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ ተለያይነት እንዳለ ታውቋል፡፡ የየኪ ወረዳ ቡና የወንፊት መጠኑ ከፍተኛ (97.67) ሲሆን ሜኒትጎልዲያ ወረዳ አነስተኛ (95.33) መሆኑ ተለይቷል፡፡ የመቶ ቡና ፍሬ ክብደትን በሚመለከት የአንድራቻ ወረዳ ከፍተኛ (18.81 gm) እንዲሁም የሸኮ ወረዳ ዝቅተኛ ክብደት (16.20 gm) አሳይቷል፡፡ በጥሬ ቡና ግምገማ ውጤት ሜኒትሻሻ ወረዳ ከፍተኛ (36.53) ሲያገኝ ደቡብ ቤንች አነስተኛ (35.28) ውጤት አግኝቷል፡፡ ከፍተኛ (49.81) የቡና ጣዕም ውጤት በአንድራቻ ወረዳ ሲገኝ በየኪ ወረዳ አነስተኛ (43.33) የሆነ ውጤት ተገኝቷል፡፡ በአጠቃላይ የጥሬና ጣዕም ትንተና አንድራቻ ወረዳ ከፍተኛ ውጤት (86.23) ሲያስመዘግብ የኪ ወረዳ አነስተኛ (78.83) የሆነ ውጤት አግኝቷል፡፡ ከ85.00 በላይ የቡና ናሙናዎች 80.00 ከመቶ በላይ የሆነ አጠቃላይ ጥራትና ጣዕም ውጤት ያገኙት ስለሆነ ስፔሻሊቲ ቡና መሆን እንደሚችሉ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በአጠቃላይ በጥናት የቡና ጣዕም ባህሪያት ያገኙት ከተለያዩ የአፈር ከአካባቢው የአየር ጠባይ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት እንዳላቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪ አዲስ የቡና ጣዕም የማር ቃና ያለው ቡና በቤንችማጂና ሸካ ዞን ተገኝቷል፡፡ Abstract The Southwestern part of Ethiopia is believed to be the origin of Arabica coffee which possesses the country to have the largest diversity in coffee genetic resources. Coffee quality determines the relative price as well as the usefulness of a given quantity of coffee. Therefore, the experiment was conducted to evaluate the coffee quality of BenchMaji and Sheka zones (BMSZs) coffee producing areas and their correlation with soil and environmental variables. The experiment was laid out in Nested design with three replications. Kebeles were nested in each district and three farms in each Kebele were used as replication. One hundred sixty two coffee samples were collected and evaluated for green bean physical and cup quality traits by professional certified coffee tasters at the Jimma Agricultural Research Center, Ethiopia. Coffee physical quality (screen size, hundred bean weight, shape & make the color, and total raw quality); cup quality attributes (aromatic intensity, aromatic quality, acidity, astringency, bitterness, body, flavor, and overall cup quality) and total cup and total coffee quality were highly significant (P ≤ 0.01). The Maximum mean value for screen size was recorded for Yeki (97.67) and the minimum was recorded for Menitgoldiya (95.33). The maximum mean value for the hundred bean weight was recorded for Anderacha (18.81gm) and the minimum (16.20 gm) was recorded for the Sheko district. Similarly, the maximum total raw quality was recorded at Menitshasha (36.53) whereas the minimum was scored in SouthBench (35.28). Anderacha district had got maximum value (49.81) of total cup quality and minimum value (43.33) was achieved at Yeki district. Based on the total coffee quality result Anderacha revealed a maximum value (86.23) and a minimum value of 78.83 recorded at Yeki district. More than Eighty-five percent (85%) evaluated coffee samples scored 80 points and above the mean value of total coffee quality qualifying them as specialty coffee. Generally, this study showed the presence of variation for coffee quality attributes and statistically significant correlations of coffee quality with soil and environmental factors. In addition, the results revealed that the existence of a unique honey flavor.
አህፅሮት\r\n \r\nይህ ጥናት የተዘጋጀው የባክቴሪያ እና የፈንገሶች ፎስፌት ማዳበሪያ ቀማሪነትና የአሟሚነት ብቃታቸውን መገምገም፣ የቡናን ምርታማነት አመላካች ባህርይ በሆነው የቡና ችግኝ ዕድገት ላይ በቡና ችግኝ ማፊያ ጣቢያ ደረጃ መፈተሽና አጅግ በጣም ጥሩ ብቃት ያሳዩትን መምረጥ ነበር። ጥናቱ የተከናወነው ከየካቲት እስከ ነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም. በጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል የቡና ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ በመጠቀም ነበር። ይህ ሙከራ የተከናወነው ፍፁም በዘፈቀደ አሠራር እያንዳንዱን ተጠኝ በሶስት ቅጅ በመደጋገም ነበር። ሙከራው 4 ስብስቦች ነበሩት፣ 1ኛው ስብስብ ሁለት ምድብ ያለው ፎስፌት ማዳበሪያ አሟሚ ባክቴሪያና ፈንገሶች ምድብ እና ፎስፌት ማዳበሪያ ከፎስፌት አሟሚ ባክቴሪያና ፈንገሶች ጋር የተጣመረ ምድብ፣ 2ኛው ስብስብ 3ባክቴሪያዎችና 3ፈንገሶች እና ሁለት ደረጃ ያለው ፎስፌት የተጣመረበት፣ 3ኛው ስብስብ በነጠላ 6ቱ ፎስፌት ቀማሪ ባክቴሪያና ፈንገሶች 1.5 ኪ.ግ አፈር ከ300ግራም ቨርሚኮምፖስት ጋር የተደባለቀ፤ 3ኛው ስብስብ ባለ2 ፋክቶሪያል ሙከራ ሆኖ (3 ደረጃ ያላቸው ፎስፌት ቀማሪ ባክቴሪያና ፈንገሶች እና 3 ደረጃ ያላቸው ፎስፌት ቀማሪ ባክቴሪያና ፈንገሶች ከቨርሚ ኮምፖስት ጋር የተጣመረበት) ነበር። ሁሉም የሙከራ ስብስቦች ነጋቲቭ እና ፖዘቲቭ ማነፃፀሪያ የነበራቸው ሲሆን ስብስብ 3 እና 4 በተጨማሪ ቨርሚኮምፖስት ብቻውን እንደማነፃፀሪያ ነበራቸው። ባክቴሪያና ፈንገሶች ከፎስፈት ማዳበሪያ ጋር ሲጣመሩ የላቀ ትርጉም ያለው በተክሎች ዕድገት ላይ አሳይቷል። በተጨማሪም RSCF1.19 ከ3ቱ ባክቴሪያዎች (RCHVCB1, RScB1.19, RMaB2.11) ጋር ተዋህደው በአንድ ላይ ፎስፌት ማዳበሪያ ጋር ሲዘሩ በቡና ችግኝ ዕድገት ላይ እጅግ የላቀ ውጤት ተመዝቧል። በአጠቃላይ አብላጫ ያለው የተክሎች ዕድገት ባህሪይ መለኪያ የሆኑ ነገሮች በነጠላና በጥምረት አጨማመር ጊዜ ከቨርሚኮምፖስት ጋር በመጣመሩ ምክንያት ከነገቲቭና ፖዘቲቭ ማነፃፀሪያ ጋር ሲወዳደር ጭማሪ ዕድገት አሳይቷል። በጥቅሉ ትርጉም አዘል ውጤት ያልሆነ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ N,P እና K አጠቃቀም በተፈጥሮ ማዳበሪያ ቀማሪ ባክቴሪያ፣ ፈንገሶችና ሰው ሰራሽ ፎስፌት ማዳበሪያ ጥምረት ጊዜ ከነገቲቭና ፖዘቲቭ ማነፃፀሪያ ጋር ሲወዳደር ብልጫ ያለው ውጤት ተመዝግቧል። ቨርሚኮምፖስት ከRSCF1.19 እና RLVCF2 ፈንገሶች ጋር ሲጣመሩ እጅግ የገዘፈና ጤናማ የሆነ የአረቢካ ቡና ችግኝ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አፈር ላይ ለማሳደግና ለማምረት የተመረጠ ሆኖ ተገኝቷል።\r\n \r\n \r\nAbstract\r\n \r\nThis study was designed to evaluate the efficiency, select the best performing bacteria and fungi isolates for phosphate solubilization, and yield attributes of coffee seedlings under nursery conditions. The study was conducted at Jimma Agricultural Research Center from February to August 2019, in plastic pots. This study was carried out in CRD in three replications per treatment. The experiment has 4 sets where set 1 had the bio-inoculant factors and phosphate factor combined factorially. Set 2 had 3 factors (3PSF, 3PSB, and 2 p levels) in factorial combinations. Set 3 has a single factor (the 6 inoculants under basal VC (300g/1.5kg soil). Set 4 was a two factor trial: PSF (3 levels) and PSB (3 levels) combined factorially under basal VC. All sets had negative and positive (rec. NP) controls, and set 3 and 4 had sole VC as the additional control unit. Bio-inoculant and phosphate combination were significantly responded to all growth attributes. Moreover, co-inoculation of RSCF1.19 with three bacterial isolates (RCHVCB1, RScB1.19, and RMaB2.11) in combination with phosphate led to significantly higher tested growth parameters. A similar increase in growth attributes was observed in both single and dual inoculation due to VC used when compared with both positive and negative control. Non-significant but higher NPK-uptake was observed in a combination of bio-inoculants and phosphate fertilizer compared to the positive and negative control. The combination of VC with RSCF1.19 and RLVCF2 fungal isolates can be recommended as bio-inoculants for solubilizing inorganic phosphate and to obtain vigor and healthier coffee seedlings in the southwest soil of Ethiopia for coffee Arabica cultivation.
አህፅሮት ይህ የምርምር ሥራ በመስኖ በሚመረት ሽንኩርት ላይ በጣም ውጤታማ የውኃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ለመምረጥ እና የውኃ ምርታማነትን ለማሻሻል በደብረ ዘይት የግብርና ምርምር ማዕከል የተካሄደ ነው፡፡ ሙከራው የተካሄደው በሶስት የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴዎች እና በሶስት አፈር የመሸፈን ዘዴዎች በተከፋፈለ መደብ ውስጥ ነው፡፡ ከጥናቱ ውጤት እንደተገኘው የተለያዩ የቦይ መስኖ ዘዴዎች በሽንኩርት ምርትና ውኃ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በተጨማሪም፣ የሽንኩርት ዕድገት፣ የምርት እና ምርታማነትን ከማሻሻል አንፃር የተለያዩ የትነት መከላከያ ልባስ ዘዴዎች መካከል የታየው ተፅዕኖ ከፍተኛ እንዳልሆነ ውጤቱ አሳይቷል፡፡ ይሁንና በጣም ከፍተኛ የሆነ የሽንኩርት ምርት (39.5 ቶን በሄክታር) በተለመደው መደበኛ የመስኖ ዘዴ የተመዘገበ ሲሆን ተለዋጭ የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ (34.3 ቶን በሄክታር) ምርት በማስገኘት በሁለተኛነት ተመዝግቧል፡፡ ሆኖም ከፍተኛ የውኃ አጠቃቀም ውጤታማነት (9.7 ኪ.ግ/ኩዩቢክ ሜትር) የተገኘው በተለዋጭው የመስኖ ዘዴ ምክንያት ሲሆን ይህም ከተለመደው የመስኖ ውኃ አሰጣጥ የውኃ ፍጆታ (5.7 ኪግ/ኩዩቢክ ሜትር) ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም የሽንኩርት ምርት እና የውኃ ምርታማነት ከተለምዶ የመስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴ ከ18 እስከ 22 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ተለዋጭ የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴ ደግሞ ከተለመደው እስከ 42 በመቶ የውሃ አጠቃቀምን ምርታማነትን አሳይቷል፡፡ ስለዚህ የመስኖ ውሃ እጥረት ባለባቸው አከባቢዎች ተለዋጭ የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴ የአፈርን በፕላስቲክ የመሸፈን ዘዴን በማቀናጀት በተለያየ ምክንያት የሚባክነውን የመስኖ ውኃ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል የተገኘው ውጤት ያሳያል፡፡ Abstract The aim of this study was to select the most effective water-saving techniques and improve the water use efficiency of irrigated onions under limited agricultural water availability. The experiment was conducted in split plot design with three types of furrow irrigation methods and mulch types in three replications. The result revealed that different types of furrow method and mulch type are significantly affected (p<0.01) marketable yield of onion. It has been observed that the significantly highest marketable yield (39.5 t/ha) of onion was recorded due to CFI and followed by AFI method (34.3 t/ha). However, the highest WUE (9.7 kg/m3) was obtained due to AFI method when compared with the CFI method of 5.7 kg/m3. Hence, there was 18 to 22% increment of marketable yield and WUE of the onion by applying mulching over the non-mulching condition and also 42% improvement of WUE by using AFI over the conventional furrow method. Therefore, for maximizing the marketable yield of onion under limiting irrigation water resource, irrigation of onion could be done with AFI method with plastic mulch application to minimize evaporation loss and maximize water productivity of onion for similar agro-ecology and soil type.
አህፅሮት ፎስፈረስ የተባለው ንጥረ-ነገር በብዛት በአፈር ውስጥ የሚገኙ ዕፅዋቶች በቀላሉ መጥጠው ሊጠቀሙበት በማይችሉት ጠጣር መልክ የሚገኝ ነው፡፡ ይሄም የሚሆነው በአፈር ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ንጥረ-ነገሮች ጋር ጠንካራ ጥምረት በመፍጠር በቀላሉ በዉኃ የማይሟሟ ውህድ ስለሚፈጥር ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ተክሎች የሚገጥማቸውን የፎስፈረስ ንጥረ-ነገር እጥረት ለማሻሻል ከሚወሰዱ አማራጭ መፍትሄዎች ውስጥ የፎስፈረስ ውሁድ አሟሚ ደቂቅ አካላት ለረጅም ጊዜ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በመጠናት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሄም ጥናት ያተኮረው እነዚህን ደቂቅ አካላት በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ ኮምጣጣ አፈር ከመኖሩ ጋር ተያይዞ ያለውን ለዕፅዋቶች በቀላሉ ሊመጠጥ የማይችለውን የፎስፈረስ ንጥረ- ነገር በማሟት ለዕፅዋቶች እንዲቀርብ በማስቻል በአኩሪ አተር ምርት ላይ ያለውን ውጤታማነት ለመገምገም ነው፡፡ ለዚህም ጥናት ከአኩሪ አተር ስር ጋር ከተያያዘ አፈር አምስት የፎስፈረስ ውሁድ አሟሚ ደቂቅ አካላት በቤተ ሙከራ ውስጥ ተለይተዋል፡፡ የነዚህም ደቂቅ አካላት ከካልሼም፣ ከብረት እና ከአልሙኒየም ጋር ውሁድ የፈጠረን ፎስፈረስ የማሟሟት ብቃታቸው ተጠንቷል፡፡ በተጨማሪም የተወሰነ የዘረ-መላቸውን አካል (16S-23S rRNA region) በመጠቀም የደቂቅ አካላቱ የዝርያ ዓይነት ተለይቷል፡፡ ብሎም የእነዚህ ደቂቅ አካላት በምርት ላይ ሊያመጡት የሚችሉት ጭማሪ በመስክ ላይ በስድስት ቦታዎች ላይ ተግምግሟል፡፡ በጥናቱም መሠረት ደቂቅ አካላቱ ፎስፈረስን ከካልሺየም፣ ከብረትና ከአልሙኒየም ውሁድ ውስጥ የማሟት ባህሪ እንዳላቸው ተረጋግጧል፡፡ እንዲሁም የደቂቅ አካላቱ ዘረመል ሲጠና አንዱ ሲዶሞናሰ ከሚባለው የደቂቅ አካላት ዝርያ የሚመደብ ሲሆን አራቱ ደግሞ ባሲለስ ተብለው ከሚጠሩት የዝርያ ዓይነቶች የሚመደቡ መሆናቸው ተለይቷል፡፡ የመስክ ላይ የምርት ግምገማ ጥናቱ እንዳሳየው ከተለዩት ደቂቅ አካላት መካከል የሲዶሞናስ ምድብ የሆነው ደቂቅ አካል (EPS1 የሚል ስያሜ የተሰጠው) ናይትሮጅንን ከሚያክር ደቂቅ አካል (Bradyrhizobium, MAR 1495) ጋር በመሆን በአማካይ 17.2 በመቶ የአኩሪ አተር ምርት ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ይህም የምርት ጭማሪ አካባቢው እንዲጠቀም ከተሰጠው የፎስፈረስ መጠን ምክረ-ሃሳብ ግማሹን ከላይ ከተጠቀሰው ናይትሮጅን ከሚያክር ደቂቅ አካል ጋር ቀላቅለን ብንጠቀም ከምናገኘው የምርታማነት መጠን በላይ ነው፡፡ ይሄም ጥናት የፎስፈረስ አሟሚ ደቂቅ አካላት የዕፅዋቶችን የፎስፈረስ አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደምርጫ ተወስደው በቂ ጥናት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ጠቋሚ ነው፡፡ Abstract Phosphorus (P) is often found in forms that are inaccessible to plants, as it forms precipitates with cations or is locked in phosphorylated organic compounds. Phosphate solubilizing microorganisms have been considered as options to alleviate a deficiency of plant-available P in soils, and this experiment is conducted to make use of this microbial potential in Ethiopia where acid soils are rampant. Five phosphate solubilizing bacteria associated with soybean rhizosphere were isolated on culture media and their P dissolution efficiencies were quantified on solid and liquid media containing insoluble Ca, Fe, and Al. The isolates were genetically characterized using their 16S-23S rRNA region. Three of the best P dissolving strains were field evaluated in six different areas of Ethiopia. The isolates demonstrated P dissolving capacities. One of the isolates was from Pseudomonas genera while the rest were from Bacillus. Inoculation with EPS1, Pseudomonas fluorescens, in combination with Bradyrhizobium (MAR 1495), led to an average of 17.2% yield increase across 6 test locations. This was greater than the yield obtained with the application of half of the recommended inorganic phosphorus fertilizer rate plus Bradyrhizobium, MAR 1495 (average 10.4% yield increase). Phosphorus solubilizing microbes appear to provide an option for improving plant P uptake.
አህፅሮት የአየር ንብረት፣ የአፈር መረጃንና የሰብል ዕድገት ሞዴልን በመጠቀም የሰብል አያያዝን መወሰን በኢትዮጵያ አነስተኛ ነው። የጥናቱ ዓላማ CROPGRO የተባለውን የሰብል ዕድገት ሞዴል በመጠቀም በተለያዩ ቦታዎች የሰብል አያያዝን መወሰንና የምርት ልዩነትን በአርሶ አደሩና በምርምር መካከል ማቀራረብ ነው፡፡ በአጠቃላይ 432 ተጠኝዎችን አራት የባቄላ ዝርያ፣ ስድስት የዘር ወቅት፣ ሦስት የዘር መጠንና ስድስት የናይትሮጅን ማዳበሪያ መጠን ባካተተ በRCBD ዲዛይን በፋክቶሪያል አደራደር ዓመትን እንደ ድግግሞሽ በመውሰድ ሙከራው ተተንብዮል። የባቄላ ዝርያ ከዘር ወቅት ጋር ሲቆራኝ የተሻለ ምርት ይገኛል፡፡ ሰኔ አጋማሽ እስከ ሐምሌ መጀመሪያ ሳምንት ጎራ የተባለውን የባቄላ ዝርያ መዝራት በሆሳዕና፣ በቁሉምሳ፣ በመራሮና በሲናና ቦታዎች ከፍተኛ የእህል ምርት ያስገኛል። 450000 ተክል በሔክታር አንደ ቦታው የዘር ወቅት የተሻለ ምርት ይሰጣል። በአብዛኛው ቦታዎች 45 ኪሎ ግራም ናይትሮጅን የማዳበሪያ መጠን መጠቀም ከፍተኛ የእህል ምርት ይሰጣል። የጥናቱ ውጤት የሚያመላክተው የሰብል ዕድገት ሞዴል፣ የሰብል አያያዝና የሰብል ማሻሻያ ምርምርን በማጣመር ለግብርና ልማት ኢክስቴንሽን አስፈላጊውን መረጃ በመሥጠት ምርትን ባለው የሰብል ማሳ ላይ መጨመር ይቻላል። Abstract The use of crop models as decision support tools for exploring the consequences of various management decision options that interact with weather and soil factors are limited in Ethiopia. This study aimed to apply crop simulation CROPGRO-faba bean model in determining site-specific crop management practices to close the yield gaps. A total of 432 treatments consisted of four faba bean varieties with six sowing dates, three plant populations, and six nitrogen fertilizer rates were considered in the study. Randomized Complete Block Design (RCBD) with the factorial arrangement was used considering years as replications. There was significant variety by sowing date interactions in all locations. Grain yield was significantly affected by variety and sowing date. Sowing on late June to early July gave the highest grain yield with variety Gora at Hosana, Kulumsa, Meraro, and Sinana nitisols sites A plant population of 45 plants m-2 was found to be optimal depending on the sowing date and sites. The highest seed yield was obtained by applying 45kg ha-1 nitrogen fertilizer in most of the locations. The result showed the application of crop models in agronomic research, crop improvement, and incorporation of the findings provides important information to prepare extension material and increase production on the existing crop land.
AbstractThis study was conducted to evaluate the productive performances of crossbreddairy cattle at Holetta agricultural research center’s dairy farm. A total of 6685performance records were used and analyzed to determine the effect of period ofcalving, season of calving, parity and genetic group. Parameters used as indicator ofproductive performances were lactation milk yield (LMY), daily milk yield (DMY)and lactation length (LL). The GLM procedure of SAS 2004 was used for analysis.The overall least square means and standard errors for Lactation milk yield (LMY),daily milk yield (DMY) and lactation length (LL) were 2204.05 ± 21.12 kg, 6.88 ±0.05 kg and 326.69 ± 2.03 days, respectively. Result of fixed effect analysis indicatedthat calving period, genetic group and parity were significantly (p<0.001) influencedall productive traits. LMY, DMY, and LL were sensitive to seasonal variation.Comparisons among the crosses revealed a clear-cut difference among the geneticgroups. Milk production in the first generation crosses increased more compared tosecond generations. There were marked decline in performance among 50% F1(Borena dam x Holstein Friesian sire), F2 (F1 dam x F1 sire) and F3 (F2 dam x F2sire) from 2203kg of milk to 1697 and 1522 kg, respectively. The 75% firstgeneration was superior LMY compared with other genetic groups and producedabout 34.2 %, 74.3%, 94.3% and 45.9% more milk than 50% F1, F2, F3 and 75%second generations, respectively. The higher milk yield of 75% first generation and50% F1 crosses from other genetic groups could be associated with higher heterosiseffect in F1, higher milk gene in 75% and longer lactation length. Based on theproductive performances evaluation, the results of LMY, DMY, and LL for highgrade (75% first generation) in the present study revealed that performances werecontinued to increase with increasing proportion of exotic gene.